Monday to Friday: 9:000am – 05:00pm
Saturday, Sunday: Close
Email: in**@************lf.com
Phone: +251 945 795 283
ልጆች ሁልጊዜ የሚያነቡት አዲስ ነገር እንዲኖራቸው፣ አብዛኛውን ጊዜ በየሁለት ሳምንቱ አዳዲስ መጻሕፍትን በመደበኛነት እንጨምራለን።
ፋኖስን በኮምፒውተር፣ በታብሌት፣ እንዲሁም በስማርት ስልኮች ላይ በቀላሉ መጠቀም ይቻላል። የተሻለ ፍጥነት እና ጥራት ለማግኘት ደግሞ እንደ ክሮም (Chrome)፣ ሳፋሪ (Safari)፣ ወይም ኤጅ (Edge) ያሉ ዘመናዊ ብራውዘሮችን ቢጠቀሙ ይመረጣል።
አዎ ይቻላል፤ ነገር ግን አፑ የሚያስቀምጠው የአንዱን ልጅ የንባብ እድገት እና መረጃ ብቻ ነው። የእያንዳንዱን ልጅ ንባብ ለየብቻ መከታተል ከፈለጉ ግን ለእያንዳንዳቸው የተለያየ አካውንት መክፈት ያስፈልጎታል።
አይቻልም። አካውንቶች የተዘጋጁት ለአንድ ቤተሰብ አጠቃቀም ብቻ ስለሆነ፣ ከቤተሰብዎ ውጪ ለሌላ ሰው አሳልፎ መስጠት ክልክል ነው።
የሀገር ውስጥም ሆነ የውጭ ሀገር የክፍያ አማራጮችን እንቀበላለን። ክፍያዎን በቻፓ (Chapa)፣ በክሬዲት/ዴቢት ካርዶች፣ እንዲሁም በሞባይል ባንኪንግ በቀላሉ መፈጸም ይችላሉ።
አዎ፣ በማንኛውም ጊዜ ምዝገባዎን ማቋረጥ ይችላሉ። ገንዘብዎን በተመለከተ፣ በመጀመሪያዎቹ ጥቂት ቀናት ውስጥ ባለን የገንዘብ መመለሻ ፖሊሲ (Refund Policy) መሰረት ተመላሽ ይደረግልዎታል።
አብዛኛዎቹ መጻሕፍቶቻችን የተዘጋጁት ለአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ነው፤ ነገር ግን የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችንም ሊጠቅሙ የሚችሉ መጻሕፍትን አካተናል።
መጻሕፍቱን ፕሪንት አድርጎ በወረቀት ማውጣት አይቻልም። ነገር ግን ኢንተርኔት ባለበት ቦታ ዳውንሎድ አድርገዋቸው፣ በኋላ ኢንተርኔት በሌለበት ሰዓት (Offline) ገብተው ማንበብ ይችላሉ።
አዎ፣ ያለምንም ጥርጥር! ሁሉም መጻሕፍት ትምህርት ሰጭ እና ደህንነታቸው የተረጋገጠ ነው። እያንዳንዱ መጽሐፍ ለልጆች ዕድሜ በሚመጥን መልኩ በጥንቃቄ የተመረጠ ነው።
መጻሕፍቱን የምናመጣው ታማኝ ከሆኑ አሳታሚዎች፣ ከትምህርት ባለሙያዎች እና ከራሳችን የጸሐፊዎች ቡድን ነው።
በወር 200 ብር ብቻ በመክፈል የመጠቀም ይችላሉ። በአንድ ጊዜ የዓመት መክፈል ለሚፈልጉ ደግሞ ቅናሽ ይኖራል።
አዎ፣ በአሁኑ ሰዓት በእንግሊዝኛ፣ በአማርኛ፣ በትግርኛ እና በኦሮምኛ ቋንቋዎች የተዘጋጁ መጻሕፍት አሉን። በቅርቡ ደግሞ ተጨማሪ ቋንቋዎችን እናካትታለን።
አዎ፣ ልጆች እያነበቡ አብረው ማዳመጥ እንዲችሉ ብዙዎቹ መጻሕፍት የራሳቸው የድምጽ ትረካ አላቸው።
አዎ፣ ማየት የተሳናቸው ልጆች በድምጽ ትረካ (Audiobook) አገልግሎታችን፣ እንዲሁም ስክሪን አንባቢ (Screen reader) ቴክኖሎጂን በመጠቀም በፋኖስ መጻሕፍት መዝናናት ይችላሉ።